ጋናዊው የተከላካይ አማካይ አዞዎቹን ተቀላቀለ

አርባምንጭ ከተማ ሁለተኛ ፈራሚውን የሀገር ውጪ ተጫዋች አድርጓል፡፡

ከቀናት በፊት የአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪን ውል ያደሰው እና ተከላካዩ አዩብ በቀታን የግሉ ያደረገው አርባምንጭ ከተማ ጋናዊውን የተከላካይ አማካይ ኢማኑኤል ላሪዬን በአንድ ዓመት ውል ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል፡፡

ከአምስት ዓመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ በኋላ ለድሬዳዋ ከተማ ተጫውቶ የነበረው እና ወደ ሀገሩ ጋና ተመልሶ ለኸርትስ ኦፍ ኦክ ሲጫወት የነበረው አማካይ የተጠናቀቀውን የውድድር ዓመት ደግሞ በመከላከል ያሳለፈው ሲሆን ከሰዓታት በፊት የአዞዎቹ አባል መሆኑን ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ አሳውቋል፡፡