አርባምንጭ ከተማ ከመስመር ተከላካዩ ጋር በስምምነት ተለያይቷል

የአዞዎቹ የግራ መስመር ተከላካይ ከክለቡ ጋር ቀሪ አንድ ዓመት እያለው በስምምነት ተለያይቷል።

ከአርባምንጭ ከተማ ጋር ከከፍተኛ ሊጉ በመነሳት ወደ ፕሪምየር ሊጉ እንዲገባ ካስቻሉ ተጫዋች መካከል የግራ መስመር ተከላካዩ ተካልኝ ደጀኔ ይጠቀሳል፡፡ ላለፉት አምስት ዓመታት በክለቡ ቆይታ የነበረው የቀድሞው የደደቢት እና የኢትዮጵያ ቡና ተጫዋች በአዞዎቹ ቤት ቀሪ የአንድ ዓመት ውል የነበረው ቢሆንም ለክለቡ ባስገባው የልቀቁኝ ደብዳቤ መነሻነት በጋራ ስምምነት ከክለቡ ጋር መለያየቱ ታውቋል፡፡

ተጫዋቹም ቀጣይ ማረፊያውን ለማግኘት ስለመቃረቡ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡