ሲዳማ ቡና አማካይ ክፍሉን በማጠናከሩ ገፍቶበታል

ከአቤል እንዳለ በመቀጠል በኢትዮጵያ ቡና የምናውቀው ሌላኛው አማካይ ወደ ሲዳማ ቡና አምርቷል።

ዘንድሮ ሊጉን በደረጃ ሰንጠረዡ ሦስተኛ ላይ ተቀምጦ ያጠናቀቀው ሲዳማ ቡና እንዳለ ከበደ እና ሙሉቀን አዲሱን እንዲሁም ደግሞ ከሰዓታት በፊት አቤል እንዳለን አዳዲስ ተጫዋቾች አድርጎ ማስፈረሙ ይታወሳል፡፡ አመሻሹን ደግሞ የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹን ዊሊያም ሰለሞንን አራተኛ ፈራሚው አድርጎታል፡፡

በኢትዮጵያ ወጣቶች እና ስፖርት አካዳሚ መነሻውን ያደረገው እና በመከላከያ እንዲሁም ያለፉትን ሦስት ዓመታት በኢትዮጵያ ቡና በመጫወት ያሳለፈው አማካዩ በኢትዮጵያ ቡና ቤት የሚያቆይ ውል ቢኖረውም ከሰሞኑ በስምምነት ከተለያየ በኋላ ለቀጣይ ሁለት ዓመታት ማረፊያውን ሲዳማ ቡና አድርጓል።