ኢትዮጵያ መድን ተጨማሪ የመስመር ተከላካይ አስፈርሟል

ወደ ዝውውሩ በመግባት ቡድኑን እያጠናከረ የሚገኘው ኢትዮጵያ መድን የግራ መስመር ተከላካይ ማስፈረሙ ታውቋል።

እንደ አዲስ ቡድኑን እያዋቀረ የሚገኘው ኢትዮጵያ መድን ከሰዓታት በፊት የቀኝ መስመር ተከላካዩ አብዱልከሪም መሐመድን ማስፈረሙ ሲታወቅ አሁን ደግሞ የግራ መስመር ተከላካዩ ተካልኝ ደጀኔን የግሉ ማድረጉን አረጋግጠናል።

በደደቢት ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና አርባምንጭ ከተማ ተጫውቶ ያሳለፈው እና ከሰሞኑ ቀሪ የአንድ ዓመት ውል እያለው በስምምነት ከአዞዎቹ ጋር እንደተለያየ የሚታወቀው ተካልኝ ደጀኔ ለአንድ ዓመት የሚያቆየውን ስምምነት ከኢትዮጵያ መድን ጋር መፈፀሙ ታውቋል።