ፋሲል ከነማ አማካይ አስፈርሟል

ከዚህ ቀደም ተከላካይ እና አጥቂ ስፍራ ላይ አዳዲስ ተጫዋቾችን ያስፈረሙት አፄዎቹ የመሀል ሜዳ አማራጫቸውንም አስፍተዋል።

የዘንድሮውን የውድድር ዘመን በሁለተኛነት ያጠናቀቁት ፋሲል ከነማዎች ለከርሞው የሚጠቀሙበትን ቡድን በአዲስ ፈራሚዎች ማጠናከር ቀጥለዋል። በዚህ ሂደት ውስጥ ዛሬ የክለቡ አምስተኛ ፈራሚ በመሆን ቡድኑን የተቀላቀለው አማካዩ ታፈሰ ሰለሞን ሆኗል።

ከዚህ ቀደም በኒያላ ፣ አል አህሊ ሸንዲ ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ፣ ሀዋሳ ከተማ እንዲሁም በቅርብ ዓመታት በኢትዮጵያ ቡና ቤት የሚታወቀው የአጥቂ አማካዩ ከመናፍ ዐወል ፣ ወንድምአገኝ ማርቆስ ፣ ተስፋዬ ነጋሽ እና ሀብታሙ ገዛኸኝ በምቀጠል ወደ ፋሲል ያመራ ተጫዋች ሆኗል። ከበዛብህ መለዮ እና ሱራፌል ዳኛቸው ጋር አብሮ የቀጠለው ፋሲል ከነማ በታፈሰ መምጣት የአማካይ ክፍሉን የፈጠራ አማራጭ ይበልጥ አስፍቷል።