መስዑድ መሐመድ ወደ ቀድሞ ክለቡ ሊመለስ ነው

የውድድር ዓመቱን በጅማ አባ ጅፋር ያሳለፈው መስዑድ መሐመድ ወደ ቀድሞ ቤቱ ሊመለስ እንደሆነ ተሰምቷል።

በ2003 ኢትዮጵያ ቡና በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ የሊጉን ዋንጫ እንዲያነሱ ካስቻሉ ድንቅ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የነበረው መስዑድ መሐመድ ዳግመኛ በኢትዮጵያ ቡና መለያ ሊጫወት ነው። በወጣቶች እየተገነባ ያለው ቡድናቸውን ብስለት ባለው መስዑድ መሐመድ እንዲመራ በማሰብ አዲሱ የኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ የቅዳቸው አካል ያደረጉት መሆኑ ሲታወቅ ክለቡ እና መስዑድ ድርድር መጀመራቸውንም ሶከር ኢትዮጵያ ለማወቅ ችላለች።

በቅርብ ቀናትም ድርድሩ ፍሬ አፍርቶ መስዑድ መሐመድ ወደ ኢትዮጵያ ቡና የመመለሱ ዜና ይፋ ይሆናል ተብሎም ይጠበቃል።

ባለ ብዙ ልምዱ መስዑድ በኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ በኢትዮጵያ ቡና እና በጅማ አባ ጅፋር ተጫውቶ ማሳለፉ አይዘነጋም።