ፈረሰኞቹ የተከላካያቸውን ውል አራዝመዋል

በበርካታ ክለቦች ሲፈለግ የነበረው የመስመር ተከላካይ ከክለቡ ጋር ለመቆየት ውሉን አድሷል።
ረመዳን የሱፍ ፣ ቢኒያም በላይ እና ዳዊት ተፈራን ወደ ቡድናቸው ቀላቅለው የአቤል ያለው እንዲሁም የአብስራ ተስፋዬን ውል ያደሱት የወቅቱ የሊጉ ዋንጫ አሸናፊዎቹ ቅዱስ ጊዮርጊሶች ከደቂቃዎች በፊት የመስመር ተከላካያቸው ሔኖክ አዱኛል ውል ለተጨማሪ ዓመት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የቀድሞ የድሬዳዋ ከተማ እና ጅማ አባ ጅፋር ተጫዋች የነበረው ሔኖክ ቅዱስ ጊዮርጊስን ከ2011 ጀምሮ ሲያገለግል እንደነበር አይዘነጋም። ተጫዋቹ ከላይ እንደገለፅነው ዘንድሮ ከፈረሰኞቹ ጋር የሊጉን ዋንጫ ከማንሳቱ በፊትም ከጅማ ጋር ቻምፒዮን ሆኖ ነበር። ሔኖክ ባህር ዳር ከተማ እና መከላከያን ጨምሮ በሌሎች ክለቦች ሲፈለግ የነበረ ቢሆንም በፈረሰኞቹ መለያ ለተጨማሪ ሁለት ዓመት ለመቆየት ውሉን ማደሱ ታውቋል።