ወላይታ ድቻ አማካይ አስፈረመ

የጦና ንቦቹ ሁለተኛ ፈራሚያቸው በኃይሉ ተሻገር ሆኗል፡፡

የአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያምን ውል ከሰሞኑ ካራዘመ በኋላ የክለቡን ነባር ተጫዋቾች መሳይ ኒኮል ፣ ደጉ ደበበ እና ንጋቱ ገብረሥላሴን ውል ያደሰው እና የሳሙኤል ተስፋዬን ዝውውር የፈፀመው ወላይታ ድቻ አማካዩ በኃይሉ ተሻገርን የቡድኑ ሁለተኛ ፈራሚ አድርጎታል።

ከኢትዮ ኤሌክትሪክ የታችኛው ቡድን ከተገኘ በኋላ ለዋናው ቡድን ግልጋሎት በመስጠት ከፕሪምየር ሊጉ ጋር የተዋወቀው አማካዩ በመቀጠል በሀድያ ሆሳዕና እና የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን በወልቂጤ ከተማ ቆይታ በማድረግ ቀጣዩን አንድ ዓመት ወላይታ ድቻ ለማሳለፍ በዛሬው ዕለት ፊርማውን አኑሯል፡፡