አርባምንጭ ከተማ ከከፍተኛ ሊጉ አንድ አጥቂ አስፈርሟል

የአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪን ውል በማደስ ወደ ዝውውሩ የገባው አርባምንጭ ከተማ አንድ አጥቂ ማስፈረሙ ታውቋል።

አርባምንጭ ከተማ ወደ ዝውውሩ ገበያ በመግባት ተከላካዩ አዩብ በቀታን እና ጋናዊውን የተከላካይ አማካይ ኢማኑኤል ላሪዬን ማስፈረሙ ይታወቃል። ዛሬ ደግሞ በከፍተኛ ሊግ በምድብ ለ ጥሩ እንቅስቃሴ ያሳየውን አጥቂ ከቤንች ማጂ ቡና አስፈርመዋል።

ለሁለት ዓመት ፊርማውን ያኖረው አጥቂው ወንድማገኝ ኬራ አብዛኛው የእግርኳስ ህይወቱን በቤንች ማጂ ቡና ያሳለፈ ሲሆን ለአርባምንጭ ከተማ መፈረሙን ተከትሎ ሁለተኛ ክለቡን ያገኘ ይሆናል።