ሲዳማ ቡና የቀድሞው አማካዩን ዳግም አግኝቷል

አማካዩ አበባየው ዮሐንስ ወደ ቀድሞ ክለቡ ሲዳማ ቡና የተመለሰበትን ዝውውር ፈፅሟል፡፡

ከአሰልጣኝ ወንድማገኝ ተሾመ ሹመት በኋላ ወደ ተጫዋቾች ዝውውር በመግባት እንዳለ ከበደ ፣ ሙሉቀን አዲሱ ፣ አቤል እንዳለ እንዲሁም ከሰዓታት በፊት ፊሊፕ ኦቮኖ ፣ አንተነህ ተስፋዬ እና ፀጋዬ አበራን የግሉ ያደረገው ሲዳማ ቡና አማካዩ አበባየው ዮሐንስን ከአንድ ዓመት በኋላ በድጋሚ ወደ ክለቡ ቀላቅሎታል፡፡

የቀድሞው የደቡብ ፓሊስ እና ስልጤ ወራቤ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች የነበረው አበባየው የተጠናቀቀውን የውድድር ዓመት ረዘም ያለ ጊዜ ያሳለፈበትን ሲዳማ ቡናን በመልቀቅ ወደ ሀድያ ሆሳዕና አቅንቶ ያሳለፈ ሲሆን በድጋሚ ከአንድ ዓመት ቆይታ በኋላ በሁለት ዓመት ውል ዳግም ወደ ቀድሞ ክለቡ መመለሱ ታውቋል።