ለገጣፎ ለገዳዲ ወደ ዝውውሩ ገብቷል

በቀጣይ ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሚሳተፈው ለገጣፎ ለገዳዲ የመጀመሪያ አዲስ ፈራሚውን አግኝቷል።

ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ወደ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ለመጀመሪያ ጊዜ ያደገው ለገጣፎ ለገዳዲ የአሰልጣኝ ጥላሁን እና የነባር ተጫዋቾችን ኮንትራት ከማራዘሙ በፊት የመጀመሪያ አዲስ ተጫዋቹን በይፋ አስፈርሟል፡፡

የአብቃል ፈረጃ የመጀመሪያው የለገጣፎ ፈራሚ ሆኗል፡፡ በኢትዮጵያ ቡና ያለፉትን ሦስት የውድድር ዘመናት በመስመር አጥቂነት እና ተከላካይነት ሲጫወት የቆየው ተጫዋቹ ለአዲስ አዳጊው ለገጣፎ የአንድ ዓመት ውልን በዛሬው ዕለት በይፋ ፈርሟል፡፡