ለገጣፎ ለገዳዲ የመስመር አማካይ አስፈርሟል

ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ወደ ዝውውር ገበያው በይፋ የገቡት ለገጣፎ ለገዳዲዎች ዛሬም ተጨማሪ አንድ ተጫዋች ወደ ስብስብባቸው ቀላቅለዋል።

ከቀናት በፊት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የነበረውን ወል ያቋረጠውን የዓብቃል ፈረጃን የመጀመሪያ ፈረሚያቸው ያደረጉት አዲስ አዳጊዎቹ ለገጣፎ ለገዳዲዎች በተመሳሳይ ከኢትዮጵያ ቡና በቅርቡ ውሉን ያቋረጠውን የመስመር አማካይ የግላቸው ማድረግ ችለዋል።

አዲስ አበባ ከተማ የእድሜ እርከን ቡድን የተገኘው እና ያላፉትን ሁለት ዓመታትን በኢትዮጵያ ቡና የቆየው የመስመር አማካዩ አላዛር ሽመልስ የአሰልጣኝ ጥላሁን መኮንንን ስብስብ በአንድ ዓመት ውል በይፋ ተቀላቅሏል።

ከሌሎች ክለቦች አንፃር በመጠኑም ቢሆን ዘግይተው ወደ ገበያ የገባው ክለቡ በቀጣይ ቀናትም የሌሎች ተጫዋቾችን ዝውውር ይፈፅማል ተብሎ ይጠብቃል።