ኢትዮ ኤሌክትሪክ ተከላካይ አስፈርሟል

ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከአራት ዓመታት በኋላ ዳግም መመለስ የቻለው ኢትዮ ኤሌክትሪክ የሀዋሳ ከተማውን ተከላካይ በይፋ የግሉ አድርጓል፡፡

ዘግየት ብለው ወደ ዝውውሩ ቢገቡም ሰለሞን ደምሴ ፣ ሙሴ ካባላ ፣ ፍቅሩ ወዴሳ፣ ኃይሌ ገብረትንሳይ፣ ጌቱ ኃይለማርያም ፣ ተስፋዬ በቀለ እና ታፈሰ ሰርካን ወደ ስብስባቸው የቀላቀሉት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች ተጨማሪ አንድ ተጫዋችን በመቀላቀል የአዳዲሶች ተጫዋቾችን ቁጥር ስምንት አድርሰዋል።

ወንድማገኝ ማዕረግ ስምንተኛው የክለቡ ፈራሚ ሆኗል፡፡ በሀዋሳ ከተማ ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች ቡድኖች ውስጥ በመጫወት የእግር ኳስ ህይወቱን የጀመረው ወጣቱ ተጫዋች በአማካይ ተከላካይነት በኋላም በተከላካይ ስፍራ ላይ ያለፉትን አምስት የውድድር ዓመታት በሀዋሳ ዋናው ቡድን ውስጥ በሊጉ በመጫወት ቆይታን አድርጎ በአንድ ዓመት ውል ኤሌክትሪክን በይፋ ተቀላቅሏል፡፡