ለገጣፎ ለገዳዲ የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር ፈፅሟል

በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ፕሪምየር ሊጉን የተቀላቀለው ለገጣፎ ለገዳዲ የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር አገባዷል፡፡

ከታችኛው የሊግ ዕርከን ክለቡን ማሳደግ ከቻለው አሰልጣኝ ጥላሁን ተሾመ ጋር ለቀጣዩም አንድ ዓመት እንደሚቀጥል የታወቀው ለገጣፎ ለገዳዲ ተጨማሪ ሁለት ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ በአንድ ዓመት የውል ዕድሜ ቀላቅሏል፡፡

የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን በሰበታ ከተማ ያሳለፈው ወጣቱ አማካይ አንተነህ ናደው እንዲሁም ከዚህ ቀደም በለገጣፎ ፣ አርሲ ነገሌ እና ያለፈውን ዓመት ደግሞ በስልጤ ወራቤ ጥሩ ቆይታ የነበረው ግብ ጠባቂው ሚኪያስ ዶጂ አዲሶቹ የለገጣፎ ፈራሚዎች ሆነዋል፡፡