ፈረሰኞቹ ከመሐል ተከላካያቸው ጋር በስምምነት ተለያዩ

ያለፉትን ዘጠኝ ዓመታት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ቆይታ የነበረው የመሐል ተከላካይ ከክለቡ ጋር በስምነት መለያየቱ ታውቋል።

አስቀድሞ ከመስመር አጥቂያቸው ቡልቻ ሹራ ጋር በስምምነት የተለያዩት የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ የሆኑት ፈረሰኞቹ አሁን ደግሞ ከመሐል ተከላካያቸው ሳላዲን በርጌቾ ጋር በስምምነት መለያየታቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለትች።

ከኢትዮጵያ መድን በ2005 መጨረሻ ቅዱስ ጊዮርጊስን በመቀላቀል ያለፉትን ዘጠኝ ዓመታት ግልጋሎት የሰጠው ሳላዲን ከፈረሰኞቹ ጋር አምስት የሊጉን ዋንጫ ያነሳ ሲሆን የአንድ ዓመት ቀሪ ኮንትራት እየቀረው በስምምነት ተለያይቷል።