የዐፄዎቹ የታዛኒያ ጉዞ ስብስብ ታውቋል

ፋሲል ከነማ በአፍሪካ ኮፌዴሬሽን ካፕ ቅድመ ማጣርያ የመልስ ጨዋታውን ሲያደርግ ወደ ታንዛኒያ የሚጓዙ ተጫዋቾች ታውቀዋል።

ባሳለፍነው ሳምንት የሜዳ ላይ ጨዋታቸው 3-0 በሆነ ውጤት የብሩንዲው ቡማሙሩን በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ዕድላቸውን ያሰፉት ዐፄዎቹ የፊታችን አርብ የመልስ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

ለበዓል ለተጫዋቾቹ የቀናት ዕረፍት ከሰጡ በኋላ ትናንት በመዲናችን በመሰባሰብ የመጀመርያ ልምምዳቸውን ካከናወኑ በኋላ ዛሬ በአበበ ቢቂላ ሜዳ የመጨረሻ ዝግጅታቸውን ሰርተው አጠናቀዋል። በመጀመርያው ጨዋታ መጠነኛ የግንባር መፈንከት ጉዳት አጋጥሞት ተቀይሮ የወጣው አጥቂው ፍቃዱ ዓለሙን ጨምሮ ሁሉም ተጫዋቾች በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ።

ነገ ማለዳ ላይ ወደ ታንዛኒያ የሚያቀኑት ፋሲሎች ወደ ስፍራው የሚጓዙትን የቡድኑ ተጫዋቾችን ዝርዝር ሶከር ኢትዮጵያ አግኝታለች። እነርሱም

ግብ ጠባቂዎች

ሚካኤል ሳማኪ፣ ይድነቃቸው ኪዳኔ

ተከላካዮች

ዓለምብርሀን ይግዛው ፣ አምሳሉ ጥላሁን ፣ አስቻላው ታመነ ፣ ወንድማገኝ ማርቆስ ፣ ከድር ኩሊባሊ ፣ መናፍ አወል ፣ ዳንኤል ዘመዴ እና ተስፋዬ ነጋሽ

አማካዮች

ይሁን እንደሻው ፣ አቤል እያዩ ፣ በዛብህ መለዮ ፣ ታፈሰ ሰለሞን ፣ ሱራፌል ዳኛቸው ፣ ናትናኤል ገ/ጊዮርጊስ ፣ ሽመክት ጉግሳ እና ሀብታሙገዛኸኝ

አጥቂዎች

ፍቃዱ ዓለሙ እና ጋይራ ጁፍ

ዐፄዎቹ መልስ ጨዋታ በድምር ውጤት ድል የሚቀናቸው ከሆነ በቀጣይ የቱኒዚያውን ሴፋክሲያንን እንደሚገጥሙ አስቀድሞ የወጣው መርሐ ግብር ይጠቁማል።