አርባምንጭ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ለውጧል

አርባምንጭ ከተማ ሥራ አስኪያጁን ከኃላፊነት በማንሳት በምትኩ አቶ ታምሩ ናሳን ሾሟል፡፡

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊው አርባምንጭ ከተማ በትናንትናው ዕለት የክለቡን ሥራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ዳዊት ኃይለማርያም ባስገቡት የመልቀቂያ ደብዳቤ መሰረት ከኃላፊነት በማንሳት በማንሳት በምትካቸው አቶ ታምሩ ናሳን በዋና ሥራ አስኪያጅነት መሾሙን ለሶከር ኢትዮጵያ በላከው መረጃ አመላክቷል፡፡

አቶ ታምሩ ናሳን በመምህርነት እና በደቡብ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ቢሮ ውስጥ በጤና ባለሙያነት እና ለሌሎች ኃላፊነቶች አገልግለዋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ ከ17 ፣ ከ20 እና ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ውስጥ በህክምና ባለሙያነት እንዲሁም በፕሪምየር ሊጉ የወልቂጤ ከተማ የህክምና ባለሙያ በመሆን ካገለገሉ በኋላ አዲሱ የአርባምንጭ ሥራ አስኪያጅ ሆነው ተሹመዋል።