ሲዳማ ቡና አዲስ ስራ አስኪያጅ ሾሟል

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሚካፈለው ሲዳማ ቡና በዛሬው ዕለት አዲስ ስራ አስኪያጅ ሾሟል፡፡

በ2015 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ የሚካፈለው እና ከውጤት አንፃር የወጥነት ችግር ሲስተዋልበት የሚታየው ሲዳማ ቡና ከደቂቃዎች በፊት የክለቡ ቦርድ ባደረገው ውይይት የአዲስ ስራ አስኪያጅ ሹመትን አፅድቋል፡፡ ክለቡ ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መረጃ መሠረትም አቶ አቡሽ አሰፋን በስራ አስኪያጅነት ሾሜያለሁ ብሏል፡፡ ቀደም ብሎ በቦታው የነበሩት አቶ ኤርሚያስ ተስፋዬ በግል በገጠመው ጉዳይ የተነሳ በአግባቡ ስራውን አይገኘም በሚል በምትኩ አቶ አቡሽ ስለመተካታቸው መረጃው አመላክቷል፡፡

በሊጉ የአሰልጣኝ ለውጥ በማድረግ ቀዳሚ የነበረው ክለቡ ከሰዓታት በኋላ ከመቻል ጋር የስምንተኛ ሳምንት መርሀግብሩን የሚያካሂድም ይሆናል፡፡