ሙጂብ ቃሲም ቀጣይ ጨዋታዎች ያመልጡታል

የሀዋሳ ከተማ አጥቂ ሙጂብ ቃሲም በተወሰኑ ጨዋታዎች ግልጋሎት እንደማይሰጥ ታውቋል።

ባለንበት ዓመት ሀዋሳ ከተማን በመቀላቀል በዘጠኝ የጨዋታ ሳምንታት አምስት ጎሎችን በማስቆጠር የክለቡ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ የሆነው ሙጂብ ቃሲም ጉዳት አጋጥሞታል። ተጫዋቹ ባሳለፍነው ሳምንት ቡድኑ ከፈረሰኞቹ ጋር ባደረጉት ጨዋታ እስከ 70ኛው ደቂቃ ድረስ ቢጫወትም በኋላ ላይ የወገብ ህመም አጋጥሞት ለቀናት ከልምምድ እርቆ መቆየቱ ታውቋል። ነገ ከኢትዮጵያ መድን ጋር በሚኖረው የአስረኛ ሳምንት ጨዋታም እንደማይኖር ተረጋግጧል።

የህመሙ ሁኔታ በቂ ዕረፍት እንደሚያስፈልገው በህክምና ባለሙያዎች መገለፁን ተከትሎ ተጨማሪ ጨዋታዎች እንደሚያመልጡት ለማወቅ ችለናል።