የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለተጫዋቾች ጥሪ አድርጓል

ዋልያዎቹ ለሚሳቱፉበት የቻን ውድድር ለ42 ተጫዋቾች ጥሪ መደረጉን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አሳውቋል።

በአሰልጣኝ ወበቱ አባተ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አልጄሪያ ላይ ለሚደረገው የአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) ማለፉ ይታወሳል። ፌዴሬሽኑ ከደቂቃዎች በፊት ባጋራው መረጃ አሰልጣኙ ለቅድመ ዝግጅት እንዲረዳ እና ተጫዋቾች በየክለባቸው በውድድር ላይ እያሉ ተገቢውን ክትትል እና ዝግጅት ለማከናወን እንዲረዳ ዕጩ የተጨዋቾች ዝርዝር ማቅረብ አስፈላጊ በመሆኑ ለ42 ተጫዋቾች ጥሪ ማቅረባቸውን ገልጿል። በወርሀ ጥር ለሚደረገው ውድድር ብሔራዊ ቡድኑ ከታህሳስ 18 ጀምሮ ቅድመ ዝግጅቱን እንደሚጀምር ይጠበቃል።

ጥሪ የተደረገላቸው 42 ተጫዋቾች ዝርዝር ይህንን ይመስላል፦

ግብ ጠባቂዎች

ፋሲል ገብረሚካኤል – ባህር ዳር ከተማ
በረከት አማረ – ኢትዮጵያ ቡና
ዳግም ተፈራ – መቻል
ባህሩ ነጋሽ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ዳንኤል ተሾመ – ድሬዳዋ ከተማ

ተከላካዮች

አስራት ቱንጆ – ኢትዮጵያ ቡና
ሱሌይማን ሀሚድ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ረመዳን የሱፍ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ሄኖክ አዱኛ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ዓለምብርሃን ይግዛው – ፋሲል ከነማ
ጊት ጋትኩት – ሲዳማ ቡና
አስቻለው ታመነ – ፋሲል ከነማ
ምኞት ደበበ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ብርሃኑ በቀለ – ሀዲያ ሆሳዕና
ያሬድ ባየ – ባህር ዳር ከተማ
ፍሬዘር ካሣ – ሃዲያ ሆሳዕና
ፈቱዲን ጀማል – ባህር ዳር ከተማ
ገዛኸኝ ደሳለኝ – ኢትዮጵያ ቡና

አማካዮች

አማኑኤል ዮሐንስ – ኢትዮጵያ ቡና
ጋቶች ፓኖም – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ይሁን እንዳሻው – ፋሲል ከነማ
ከነዓን መርክነህ – መቻል
መስዑድ መሐመድ – አዳማ ከተማ
በዛብህ መለዮ – ፋሲል ከነማ
ናትናኤል ሰለሞን – ኢትዮ ኤሌክትሪክ
ቢኒያም በላይ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ፍሬው ሰለሞን – ሲዳማ ቡና
ታፈሰ ሰለሞን – ፋሲል ከነማ
ፉአዓድ ፈረጃ – ባህር ዳር ከተማ

አጥቂዎች

በረከት ደስታ – መቻል
ቸርነት ጉግሳ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ይገዙ ቦጋለ – ሲዳማ ቡና
አማኑኤል ገብረሚካኤል – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ዳዋ ሆቴሳ – አዳማ ከተማ
ብሩክ በየነ – ኢትዮጵያ ቡና
ኪቲካ ጀማ – ኢትዮጵያ መድን
ዱሬሳ ሹቢሳ – ባህር ዳር ከተማ
ቢኒያም ጌታቸው – ድሬዳዋ ከተማ
ጌታነህ ከበደ – ወልቂጤ ከተማ
ሽመክት ጉግሳ – ፋሲል ከነማ
ምንይሉ ወንድሙ – መቻል
ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ – ፋሲል ከነማ