ለዋልያዎቹ የቻን ተሳትፎ የ28ተጫዋቾች ዝርዝር ይፋ ሆኗል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለሚጠብቀው የቻን ውድድር የተጫዋቾች የመጨረሻ ስብስብ ተለይቷል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቀጣዩ ወር በአልጃሪያ አስተናጋጅነት ለሚደረገው የአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮን ሺፕ ማለፉ ይታወሳል። ከቀናት በኋላ ዝግጅቱን ለሚጀምረው ቡድን ከዚህ ቀደም የ42 ዕጩ ተጫዋቾች ዝርዝር ይፋ ተደርጎ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ የተጨዋቾች ዝርዝሩ ወደ 28 ዝቅ ብሏል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከደቂቃዎች በፊት ካጋራው ዝርዝር ላይ በተመለከትነው መሰረት ወንድምአገኝ ኃይሉ ፣ አለልኝ አዘነ እና ሚሊዮን ሰለሞን ከዚህ ቀደም ከነበረው የ42 ተጫዋቾች ዝርዝር በአዲስ መልክ የተጠሩ ተጫዋቾች ሆነዋል።

ግብ ጠባቂዎች

ፋሲል ገ/ሚካኤል – ባህር ዳር ከተማ
በረከት አማረ – ኢትዮጵያ ቡና
ባህሩ ነጋሽ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

ተከላካዮች

አስቻለው ታመነ – ፋሲል ከነማ
ምኞት ደበበ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ሚሊዮን ሰለሞን – አዳማ ከተማ
ጊት ጋትኩት – ሲዳማ ቡና
ፈቱዲን ጀማል – ባህር ዳር ከተማ
ገዛኸኝ ደሳለኝ – ኢትዮጵያ ቡና
ሱለይማን ሀሚድ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ረመዳን የሱፍ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ዓለምብርሃን ይግዛው – ፋሲል ከነማ
ብርሃኑ በቀለ – ሀዲያ ሆሳዕና

አማካዮች

ጋቶች ፓኖም – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ይሁን እንዳሻው – ፋሲል ከነማ
አለልኝ አዘነ – ባህር ዳር ከተማ
መስዑድ መሐመድ – አዳማ ከተማ
ከነዓን ማርክነህ – መቻል
ወንድማገኝ ኃይሉ – ሀዋሳ ከተማ
ታፈሰ ሰለሞን – ፋሲል ከነማ
ፉዓድ ፈረጃ – ባህር ዳር ከተማ
ቢኒያም በላይ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

አጥቂዎች

ጌታነህ ከበደ – ወልቂጤ ከተማ
አማኑኤል ገ/ሚካኤል – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ይገዙ ቦጋለ – ሲዳማ ቡና
ቸርነት ጉግሳ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ኪቲካ ጀማ – ኢትዮጵያ መድን ድርጅት
ዱሬሳ ሹቢሳ – ባህር ዳር ከተማ