ኢትዮጵያ ቡና ከተከላካዩ ጋር በስምምነት ተለያይቷል

የመሀል ተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ አበበ ጥላሁን ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ቀሪ የውል ዘመን እየቀረው በስምምነት ተለያይቷል።

\"\"

ኢትዮጵያ ቡናን ለአራት የውድድር ዘመን በ2013 የውድድር ዘመን ከተቀላቀሉ ተጫዋቾች መካከል ይጠቀሳል ፤ ተከላካዩ አበበ ጥላሁን። የቀድሞው የአርባምንጭ ከተማ ፣ ሲዳማ ቡና እንዲሁም መቻል ተጫዋች በአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ የአሰልጣኝነት ዘመን ወደ ለቡናማዎቹ በመፈረም እስከ ዘንድሮ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመን አጋማሽ ድረስ በክለቡ ቆይታን ሲያደርግ ቆይቷል።

ለቀጣዮቹ አንድ ዓመት ከስድሰት ወራት ተከላካዩ አበበ በኢትዮጵያ ቡና የሚያቆየው ውል የነበረው ቢሆንም ከክለቡ ጋር በጋራ ስምሞነት መለያየቱን ሶከር ኢትዮጵያ ለማወቅ ችላለች። ከሁለት የተለያዩ ክለቦች ጋር ንግግር እንደጀመረ የሚነገርለት ተጫዋቹ በቀጣይ ወደ የትኛው ክለብ ያመራል የሚለውን ጉዳይ ይጠበቃል።

\"\"