አቶ ኢሳይያስ ጂራ በሴካፋ ምክትል ፕሬዝዳንትነት በድጋሚ ተመረጡ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ በሴካፋ በምክትል ፕሬዝዳንትነት በድጋሜ መመረጣቸው ታውቋል።

በምስራቅ እና መካከለኛው ቀጠና የሚገኙ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች የተዋቀረው ሴካፋ በዛሬው ዕለት የምርጫ ጠቅላላ ጉባኤውን ዛንዚባር ላይ አከናውኗል። በዚህ ጉባኤ ላይም የቀጠናው ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ፕሬዝዳንቶች እና ዋና ፀሐፊዎች የተገኙ ሲሆን ሀገራችንን በመወከልም አቶ ኢሳይያስ ጅራ እና አቶ ባህሩ ጥላሁን ወደ ስፍራው ተጉዘው ታድመዋል።

\"\"

በጉባኤው ላይ በተደረገው ምርጫም ከወራት በፊት የኢትዮጵያን እግርኳስ ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት በፕሬዝዳንትነት ለማገልገል የተመረጡት አቶ ኢሳይያስ በሴካፋም በነበሩበት የምክትል ፕሬዝዳንት ኃላፊነት ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት እንዲያገለግሉ በድጋሜ መመረጣቸው ይፋ ሆኗል።

\"\"

እንደ አቶ ኢሳይያስ ሁሉ የታንዛንያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የሆኑት ዋላስ ካይራም በተመሳሳይ በድጋሜ በመመረጣቸው ተቋሙን በፕሬዝዳንትነት የሚመሩ ይሆናል።