ኢትዮ ኤሌክትሪክ አጥቂ አስፈርሟል

የመስመር አጥቂው አብዱራህማን ሙባረክ የኢትዮ ኤሌክትሪክ የሁለተኛው ዙር የመጀመሪያ ፈራሚ ሆኗል።

\"\"

በኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ላይ ዳግም ከታችኛው የሊግ ዕርከን በማደግ እየተወዳደረ የሚገኘው ኢትዮ ኤሌክትሪክ አሰልጣኝ ገዛኸኝ ከተማን ከረዳት አሰልጣኝነት ወደ ዋና አሰልጣኝነት ቦታ ላይ ከሾመ በኋላ ለቀጣዮቹ ቀሪ አስራ ሰባት የሊግ ጨዋታዎች ላይ ተጠናክሮ ለመቅረብ በትናንትናው ዕለት ዝግጅት የጀመረ ሲሆን ራሱን ለማጠናከርም ወደ ዝውውሩ ጎራ ብሏል። በሊጉ ካደረጋቸው አስራ ሶስት ጨዋታዎች በ8 ነጥቦች 15ኛ ላይ የተቀመጠው ክለቡ የመስመር እና የፊት መስመር አጥቂው አብዱራህማን ሙባረክ (ግሪዳውን) በአንድ ዓመት ውል ማስፈረሙን ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ አሳውቋል።

\"\"

የቀድሞው የፋሲል ከነማ እና ወልቂጤ ከተማ ተጫዋች 2014 ላይ ወደ ድሬዳዋ በማምራት ግልጋሎትን ሰጥቷል። በዘንድሮ ዓመታት ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ቀሪ የአንድ ዓመት ውል እያለው የተለያየው ተጫዋቹ ከስድስት ወራት ክለብ አልባ ቆይታ በኋላ በይፋ ወደ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አምርቷል።