ለገጣፎ ለገዳዲ ሁለት ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል

አሠልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስን የሾመው ለገጣፎ ለገዳዲ በቋሚ እና በውሰት ውል ሁለት ተጫዋቾችን አስፈርሟል።

\"\"

በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ያደገው ለገጣፎ ለገዳዲ በ13 ጨዋታዎች ባስመዘገበው አንድ ድል እና ሦስት የአቻ ውጤት ስድስት ነጥብ ይዞ የደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ ተቀምጧል። ሊጉ ለብሔራዊ ቡድን የቻን ውድድር በሚቋረጥበት ጊዜም ክለቡ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስን በአሠልጣኝነት በመሾም ቀደም ብሎ ለሊጉ የአዳማ ቆይታ ዝግጅቱን ሲያደርግ ነበር። ዛሬ በሚዘጋው የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ደግሞ ሁለት ተጫዋቾችን ማስፈረሙን አውቀናል።

ክለቡን የተቀላቀለው የመጀመሪያው ተጫዋች የቀድሞ የጅማ አባ ጅፋር ተጫዋች ኤሊያስ አታሮ ነው። ተጫዋቹ ዓምና ወደ ሀዲያ አምርቶ የእግርኳስ ህይወቱን ቀጥሎ የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ በሌላኛው የሊጉ ክለብ ግልጋሎት ለመስጠት ፊርማውን አኑሯል።

\"\"

ሁለተኛው ተጫዋች ደግሞ የመስመር አማካይ እንዲሁም የመስመር ተከላካይ በመሆን የሚጫወተው ተስፋዬ ነጋሽ ነው። የቀድሞ የወልዲያ፣ አዳማ ከተማ እና ወልቂጤ ተጫዋች ክረምት ላይ ለፋሲል ከነማ ፊርማውን ያኖረ ሲሆን በታሰበው ልክ ክለቡን ማገልገል ሳይችል ቀርቶ በውሰት ውል ወደ ለገጣፎ ለገዳዲ አምርቷል።