ኢትዮ ኤሌክትሪክ አንድ ተጫዋች ሲያስፈርም ከአራቱ ጋር ተለያይቷል

በዝውውር መስኮቱ የነቃ ተሳትፎን እያደረገ የሚገኘው ኢትዮ ኤሌክትሪክ አማካይ ተጫዋችን ሲያስፈርም ከአራት ተጫዋቾች ጋር በስምምነት ተለያይቷል።

በዝውውር መስኮቱ እስከ አሁን አብዱራህማን ሙባረክ ፣ አማረ በቀለ እና ዮናስ ሰለሞንን ያስፈረመው ኢትዮ ኤሌክትሪክ የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ነፃነት ገብረመድህንን አራተኛ ፈራሚው አድርጎታል።

\"\"

በስሑል ሽረ ቡድን ውስጥ ረጅም ቆይታን ካደረገ በኋላ 2013 አጋማሹ ላይ ወላይታ ድቻ ለስድስት ወራት በመቀላቀል የተጫወተው እና በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በነበረው ጦርነት ያለፈውን አንድ ዓመት ከግማሽ ወራት ያህል ካለ ክለብ ከቆየ በኋላ ከሰሞኑ በአዳማ የሙከራ ጊዜን ቢያሳልፍም በስተመጨረሻ መዳረሻው ኤሌክትሪክ በአንድ ዓመት ሆኗል።

ክለቡ የተከላካዩ ማታይ ሉልን ውል ለተጨማሪ ዓመት ሲያራዝም ከአጥቂው ሔኖክ አየለ ፣ ከመስመር ተከላካዩ ሀይሌ ገብረትንሣኤ ፣ ከአማካዩ ምንያህል ተሾመ እና ግብ ጠባቂው ሰለሞን ደምሴ ጋር በጋራ ስምምነት ተለያይቷል።

\"\"