ሀዋሳ ከተማ አምስት ተጫዋቾችን ወደ ዋናው ቡድን አሳድጓል

በአሰልጣኝ ዘርአይ ሙሉ የሚመራው ሀዋሳ ከተማ በዛሬው ዕለት አምስት ተጫዋቾችን ከ20 ዓመት ቡድኑ አሳድጓል።

\"\"

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ታዳጊ እና ወጣት ተጫዋቾችን ከሚያበቁ ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው ሀዋሳ ከተማ በአሰልጣኝ ዘርአይ ሙሉ መሪነት ከአዳማ ጀምሮ በሚደረገው የሁለተኛው ዙር የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ ተጠናክሮ ለመቅረብ በማሰብ አዳዲስ ተጫዋቾችን ከተለያዩ ክለቦች ከማምጣት ይልቅ ከ20 ዓመት በታች ቡድኑ አምስት ወጣት ተጫዋችን ለማብቃት በማሰብ በዛሬው ዕለት ወደ ዋናው ቡድኑ ማሳደጉን ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ በላከው መረጃ አመላክቷል።

\"\"

በዚህም አለህኝ ዋለልኝ (ግብ ጠባቂ) ፣ ናትናኤል ሻጋሞ (አማካይ) ፣ ሲሳይ ጋቾ (ተከላካይ) ፣ ያሬድ ብሩክ (አማካይ) እና ብሩክ ታደለ (አማካይ) ወደ ዋናው ቡድን ያደጉ አምስቱ ተጫዋች ናቸው።