ለሀዋሳ ከተማ የሴቶች ቡድን የትጥቅ ድጋፍ ተደረገ

የሀዋሳ ከተማ ደጋፊዎች ማኅበር ለክለቡ የእንስቶች ቡድኑ የትጥቅ ድጋፍ አድርጓል።

\"\"

ሀዋሳ ከተማ በዘንድሮ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ውድድር ላይ የመጀመሪያውን ዙር በ25 ነጥቦች አራተኛ ደረጃን በመያዝ ማገባደዱ ይታወቃል። ቡድኑም ገና ከተቋቋመ አንድ ዓመት ባስቆጠረው የደጋፊ ማኅበሩ የትጥቅ ድጋፉ በትናንትናው ዕለት ተደርጎለታል።

በትጥቅ ርክክብ መርሐ-ግብሩ ላይ የክለቡ የቦርድ አባል እና የማኅበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ባዩ ባልጉዳ ከሌሎች የማኅበሩ አባላት ጋር በመሆን የተገኙ ሲሆን ለቡድኑ አሰልጣኞች ፣ አመራሮች እና ለተጫዋቾች የትጥቅ ድጋፉን አድርገዋል። አቶ ባዩ ማኅበሩ በአዲስ መልክ ከተቋቋመ ገና አንድ ዓመት መሆኑን አውስተው በቅርቡ ከ12 ሺ በላይ ደጋፊዎች የተሳተፉበት የሩጫ መርሐ-ግብርን እንዳደረጉ በመግለፅ ዛሬ የተደረገው ድጋፍ ጅምር መሆኑን አመላክተዋል። ጨምረውም በቀጣይ ቡድኑ የተሻለ ውጤት ካስመዘገበ ከአሁኑ በተሻለ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።

\"\"

የክለቡ አሰልጣኞች እና ተጫዋቾች ለተደረገላቸው የትጥቅ ድጋፍ አመሰግነው በሁለተኛው ዙርም የተሻለ ውጤት ለማምጣት እንደሚጥሩም ጭምር ተናግረዋል።