ለፕሪምየር ሊጉ ተጫዋቾች የሚዲያ አጠቃቀምን በተመለከተ ስልጠና ሊሰጥ ነው

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ከመልቲቾይዝ ኢትዮጵያ ጋር በመሆን ለሊጉ ተጫዋቾች ከሚዲያ አጠቃቀም ጋር የተያያዘ ስልጠና በነገው ዕለት ይሰጣል።

\"\"

የኢትዮጵያን ከፍተኛው የሊግ እርከን ውድድር የሚያስተዳድረው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር አጋሩ ከሆነው መልቲቾይዝ ኢትዮጵያ ጋር በመሆን ያለፉትን ሁለት ዓመታት ለተለያዩ የእግርኳሱ የባለ-ድርሻ አከላት ስልጠናዎችን ሲሰጥ እንደነበር አይዘነጋም። በነገው ዕለት ደግሞ ከአስራ ስድስቱም ክለብ የተመረጡ ተጫዋቾች የሚሳተፉበት ስልጠና (ወርክ-ሾፕ) በድሬዳዋ ብሉ ሰም ሆቴል እንደሚሰጥ ታውቋል።

\"\"

ይህ ስልጠና ተጫዋቾች በስፖርት (እግርኳስ)ዘርፍ በሶሻል ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪነት፣ በዲጂታል ብራንዲንግ እና ራስን ማስተዋወቅ ላይ ያተኮረ እንደሆነ ተጠቁሟል። በዚህም በነገው ዕለት ሙሉ ቀን እንደሚፈጅ የተገለፀው ስልጠና ላይ ከሁሉም ክለብ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሁለት ሁለት ተጫዋቾች እንዲገኙ ጥሪ ቀርቧል።