የዋልያዎቹ ተጋጣሚ ስብስቧን ይፋ አድርጋለች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ቀጣይ ተጋጣሚ የሆነው የጊኒ ብሔራዊ ቡድን ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርቧል።

\"\"

ዛሬ በጀመርነው የመጋቢት ወር አጋማሽ የአህጉራችን ብሔራዊ ቡድኖች ለ2023ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የምድብ ማጣሪያ ሦስተኛ እና አራተኛ ጨዋታቸውን የሚያከናውኑ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ከጊኒ አቻው ጋር ወሳኝ ፍልሚያዎችም ሞሮኮ ላይ ያከናውናል። ለእነዚህ ሁለት ጨዋታዎች የዋልያዎቹ አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ምርጫ እየተጠበቀ የሚገኝ ሲሆን የጊኒው አሠልጣኝ ካባ ዲያዋራ በበኩላቸው ለተጫቾች ጥሪ ማስተላለፋቸው ይፋ ሆኗል።

አሠልጣኙ በምርጫቸው ሦስት የግብ ዘቦች፣ ስምንት ተከላካዮች፣ ስድስት አማካዮች እና ስድስት አጥቂዎችን በአጠቃላይ 23 ተጫዋቾችን መምረጣቸው ታውቋል።

በስብስቡም በእንግሊዙ ሊቨርፑል የሚጫወተው ናቢ ኬታ እና በስፔኑ ቫሌንሲያ የሚገኘው ሞሪባን ጨምሮ በፈረንሳይ ሊግ ኧ፣ ጀርመን ቡንደስሊጋ፣ ስፔን ላሊጋ እና ቤልጂየም ሊግ የሚጫወቱ ተጫዋቾች ተካተዋል።

\"\"

ስብስቡ ከስር ተያይዟል 👇