ዋልያዎቹ ዝግጅታቸውን የሚጀምሩበት ቀን ታውቋል

መጋቢት 15 እና 18 ለሚደረጉት ሁለት ወሳኝ ጨዋታዎች ዋልያዎቹ ዝግጅታቸውን የሚጀምሩበት ቀን ይፋ ሆኗል።

\"\"

በአሠልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ሦስተኛ እና አራተኛ ጨዋታውን ከጊኒ አቻው ጋር የሚያከናውን ይሆናል። አሠልጣኙም ከቀናት በፊት በጨዋታዎቹ ግልጋሎት የሚሰጧቸውን 23 ተጫዋቾች የመረጡ ሲሆን ስብስቡም መደበኛ ዝግጅቱን የሚጀምርበትን ቀን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል።

\"\"

በዚህም ከነገ በስትያ ረቡዕ ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ተሰባስበው ዝግጅታቸውን እንደሚጀምሩ ተመላክቷል።