ዋልያዎቹ የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ሊያደርጉ ነው

ከጊኒ ጋር ሁለት ጨዋታዎች የሚጠብቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከፍልሚያዎቹ በፊት ሀገሩ ላይ የአቋም መለኪያ ጨዋታ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

\"\"

በአይቮሪኮስት አስተናጋጅነት ለሚከናወነው የ2023 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የምድብ የማጣሪያ ጨዋታዎችን እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መጋቢት 15 እና 18 ከጊኒ ጋር ወሳኝ ሦስተኛ እና አራተኛ ጨዋታዎች ይጠብቀዋል። ለእነዚህ ፍልሚያ የቡድኑ አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ለተጫዋቾች ጥሪ አቅርበው የነበረ ሲሆን ከነገ በስትያም ልምምዳቸውን የሚጀምሩ ይሆናል።

\"\"

ቡድኑ ጨዋታዎቹን ለማድረግ ወደ ሞሮኮ ከማምራቱ በፊት ደግሞ ሀገሩ ላይ የአቋም መፈተሻ መርሐ-ግብር እንደሚከውን ተመላክቷል። በዚህም ቡድኑ መጋቢት 10 ከሩዋንዳ አቻው ጋር በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም ጨዋታውን እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ገልጿል።