ብርትካናማዎቹ በይፋ አማካይ አስፈርመዋል

ከቀናት በፊት ድሬዳዋ ከተማን ሊቀላቀል እንደሆነ ዘግበን የነበረው አማካይ ዝውውሩን አገባዷል።

\"\"

በአሠልጣኝ ዮርዳኖው ዓባይ የሚመሩት ድሬዳዋ ከተማዎች በውድድር አጋማሽ የዝውውር መስኮት አንድም ተጫዋች ባያስፈርሙም የነፃ ተጫዋች ዝውውር መብትን ተጠቅመው ባለልምዱን አማካይ ዳዊት እስቲፋኖስን ለማስፈረም እንቅስቃሴ እንደጀመሩ ከቀናት በፊት ዘገባ አቅርበንበን ነበር። በ2014 ከጅማ አባጅፋር ጋር ካሳለፈ በኋላ ዘንድሮ ያለክለብ የቆየው ዳዊት እስቲፋኖስ ያሳለፉትን ቀናት ከቡድኑ ጋር ልምምድ ሲሰራ ቆይቶ በዛሬው ዕለት በይፋ ፊርማውን አኑሯል።

\"\"

ከዚህ ቀደም በድሬዳዋ ከተማ ተጫውቶ የነበረው ዳዊት ዳግም በክለቡ ለመቆየት የአንድ ዓመት ፊርማ እንዳኖረም ታውቋል። ተጫዋቹ ምናልባት ቡድኑ ዛሬ ምሽት 12 ሰዓት ከለገጣፎ ለገዳዲ ጋር ሲጫወት ወደ ሜዳ ሊገባ እንደሚችልም ሰምተናል።