የሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ የማጣሪያ ውድድር የሚደረግበት ጊዜ ታውቋል

የሴካፋ ዞን የሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ ማጣሪያ ውድድር የት እና መቼ እንደሚከወን ይፋ ሆኗል።
\"\"
ከሁለት ዓመታት በፊት የተጀመረው የአፍሪካ የሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ጥሩ ተቀባይነት በማግኘት እየተከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል። በአህጉሪቱ የሚገኙ የሊግ አሸናፊዎች በዞን ተከፋፍለው የማጣሪያ ጨዋታዎችን እያደረጉ በዋናው መድረክ ላይ የሚሳተፉ ሲሆን በሁለቱ ተከታታይ ዓመታት የሀገራችን ተወካይ የነበረው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከማጣሪያው ጉዞ መዝለል ሳይችል ቀርቶ እንደነበር አይዘነጋም። የዘንድሮ ተወካይ ማን እንደሆነ አሁን ላይ ባይታወቅም የሴካፋ ዞን የማጣሪያ ውድድር የት ሀገር እና መቼ እንደሚደረግ ይፋ ሆኗል።
\"\"
በዚህም ካፍ እንዳስታወቀው የማጣሪያው ውድድር ቀድሞ ከተያዘለት ወቅት ቀደም ብሎ ከነሐሴ 6 እስከ 20 ድረስ በዩጋንዳ ተደርጎ ዋናው ውድድር ላይ የሚሳተፈው ክለብ የሚለይ ይሆናል።