ዋልያዎቹ ጨዋታቸውን የት እንደሚያደርጉ ታውቋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከማላዊ ጋር የሚያደርገው የሜዳው ጨዋታን የሚያደርግበት ሀገር ታውቋል።

\"\"

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አምስተኛውን የምድብ ጨዋታ ሰኔ 13 (June 20) ለማከናወን ሞዛምቢክን ምርጫው ማድረጉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለካፍ አስታውቋል። ፌዴሬሽኑ ይፋ እንዳደረገው በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በሚገኙ ስታዲየሞች ላይ ለማከናወን ጥረት ቢያደርግም ሩዋንዳ ከዚህ በፊት ተፈቅዶላት የነበረ ስታዲየም ጊዜያዊ ፈቃድ በመነሳቱ ፣ ታንዛኒያ የተሰጣት ፍቃድ የብሔራዊ ቡድኗን ጨዋታ ብቻ እንድታከናወን በመሆኑ፣ ሱዳን በወቅታዊ አለመረጋጋት እንዲሁም ዩጋንዳ እና ኬንያ የተፈቀደ ስታዲየም ባለመኖሩ ምትክንያት በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ማከናወን የማይቻል በመሆኑ ኢትዮጵያ ከ ማላዊ የምታደርገውን ጨዋታ ለማከናወን ሞዛምቢክን ምርጫዋ እንዳደረገች ጠቁሟል።

\"\"