የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የግብ ጠባቂዎች አሠልጣኝ ተሹሟል

ጊዜያዊ ዋና እና ምክትል አሠልጣኝ የተሾመለት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አዲስ የግብ ዘብ አሠልጣኝ አግኝቷል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአሠልጣኝ ውበቱ አባተ እና ረዳቶ ጋር ከተለያየ በኋላ በምትኩ አዳዲስ አሠልጣኞችን ለመሾም ሲጥር የነበረ ሲሆን ከቀናት በፊትም በጊዜያዊነት ቡድኑን የሚመሩ አሠልጣኞችን መሾሙ ይታወሳል። በዚህም የፌዴሬሽኑ የቴክኒክ ዳይሬክተር ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረማርያም እና አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛውን በዋና እና ረዳት አሰልጣኝነት በቦታው ሰይሟል።
\"\"
ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መረጃ መሠረት ደግሞ የግብ ጠባቂዎች አሠልጣኝ ሆነው በቅዱስ ጊዮርጊስ እያገለገሉ የሚገኙት አሠልጣኝ ውብሸት ደሳለኝ ተሹመዋል።
\"\"
የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ውብሸት ከዚህ ቀደም በአሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ ስር የብሔራዊ ቡድኑ ግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ ሆኖ መስራቱ ይታወሳል።