ዋልያዎቹ ከሰሜን አትላንቲክ ዳርቻ ሀገር ጋር ይጫወታሉ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በክረምት ጉዞው የሚያደርገው የወዳጅነት ጨዋታ ታውቋል።

\"\"

በመጪው ክረምት የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ወደ አሜሪካ በመጓዝ ከካረቢያን ሀገራት ጋር የወዳጅነት ጨዋታዎች እንደሚያደርግ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በኩል በይፋ መገለፁ ይታወቃል።CJA newman ከተባለ ተቋም ጋር በተደረገ ስምምነት መሰረት የሚደረገው የዚህ ጉዞ አካል የሆነው የወዳጅነት ጨዋታ ከማን ጋር እና መቼ እንደሚደረግ ደግሞ ፌዴሬሽኑ ዛሬ አስታውቋል።

በዚህም መሰረት ዋልያዎቹ በሀገረ አሜሪካ በሚያደርጉት የመጀመሪያ ጨዋታ ከጉዌና ብሔራዊ ቡድን ጋር እንደሚከናወን ታውቋል። ጨዋታው ሐምሌ 01 ቀን በአሜሪካ ፊላደንፊያ በሚገኘው ሱባሩ ፓርክ ስታድየም እንደሚደረግም ፌዴሬሽኑ አስታውቋል። የሰሜን እና መካከለኛው አሜሪካ እንዲሁም የካሪቢያን እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን አካል ከሆነችው ሀገር ጋር የሚደረገው የዚህ ጨዋታ ትኬቶች ካሀኑ ለሽያጭ መቅረባቸውም ተጠቁሟል።

\"\"