የአሰልጣኞች አስተያየት| አዳማ ከተማ 0-1 ለገጣፎ ለገዳዲ

\”የሆነ ሰዓት ላይ ልናሸንፋቸው እንደምንችል ገምተን ነበር\” ዘማርያም ወልደግዮርጊስ

\”በዚህ ዓመት እንደዚህ የወረድንበት ጨዋታ የለም\” ይታገሱ እንዳለ

ዘማርያም ወልደማርያም – ለገጣፎ ለገዳዲ

ስለ ጨዋታው

ጨዋታው ጥሩ ነበር ፤ አዳማ በይበልጥ ኳስ ለመቆጣጠር እንደሚጥር ስለተረዳን ጥቅጥቅ ብለን በመልሶ ማጥቃት ለመጫወት ሞክረናል። የሆነ ሰዓት ላይ ልናሸንፋቸው እንደምንችል ገምተን ነበር ፤ ጨዋታው ያሳይ ነበር። ከዛ በፊት ያለቀላቸው ዕድሎች አምክነናል። በመጨረሻው ሰዓት አስቆጥረን ማሸነፍ ችለናል።
\"\"
ስለ እንቅስቃሴያቸው

የመጀመርያ አጋማሽ እና ሁለተኛ አጋማሽ ተመሳሳይ አልነበረም። የመጀመርያው አጋማሽ አየሩ ከባድ ስለነበር ጥሩ ተንቀሳቅሰን አቻ ለመውጣት ነበር እቅድ የያዝነው። ከዕረፍት በኋላ ግን ተጭነን ለመጫወት ሞክረናል። እውነት ለመናገር እንደወትሮ አልነበረም ቡድናችን። ታክቲካሊ ግን የተደራጀ ነበር።

ይታገሱ እንዳለ – አዳማ ከተማ

ስለ ጨዋታው

ጨዋታው ጥሩ አልነበረም። በዚህ ዓመት እንደዚህ የወረድምበት ጨዋታ የለም። በማላውቀው ምክንያት በሁሉም ረገድ የወረድንበት ፤ ደስተኛ ያልሆንኩበት ጨዋታ ነበር።
\"\"
ስለተደረጉት ለውጦች እና ቅያሪዎቹ

ዮሴፍ ጉዳት ነበረበት ፤ ዳዋ ከጉዳት መልስ ጥሩ ስለነበር ነው ቋሚ ላይ ያካተትነው።