የአሰልጣኞች አስተያየት | ድሬዳዋ ከተማ 2-1 ፋሲል ከነማ

\”ውጤቱ ይገባናል\” አሰልጣኝ አስራት አባተ

\”ጨዋታውን ማሸነፍ ነበረብን\” አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ

ብርቱካናማዎቹ ዐፄዎቹን አሸንፈው ደረጃቸው ሽቅብ ባሻሻሉበት ጨዋታ የሁለቱም ቡድን አሰልጣኞች ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል።

\"\"

አሰልጣኝ አስራት አባተ

ስለጨዋታው…

እንደ ጠበቅነው ጠንካራ ጨዋታ ነው፤ ከጠንካራ ቡድን ጋር ነው ጨዋታ ያደረግነው። ውጤቱ አስፈላጊ ስለነበር አቀራረባችንም ጠንካራ ነበር ፤ ውጤቱም ይገባናል።

ስለ ቡድኑ የመከላከል አደረጃጀት…

ዛሬ ጥሩ ነበር፤ ከተጋጣሚ ጥንካሬ አንፃር።
ዛሬ ጨዋታ አፈፃፀም ላይ ነበር ችግራችን።

ስለ ቡድኑ አሁናዊ ሁኔታ…

ቡድኑ በተቻለ መጠን ከነበረበት ችግር እንዲወጣ ከፍተኛ ጥረት አድርገናል። የተጫዋቾቹን የጨዋታ ፍላጎት በማነሳሳት እና ሜዳ ላይም ለእያንዳንዱ ጨዋታ በደምብ እንዘጋጅ ነበር። የሰራነው ሥራ አሁን ያለንበት ደረጃ እንድንገኝ አስችሎናል።

አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ

ስለጨዋታው…

ጨዋታውን ማሸነፍ ነበረብን ፤ ግን ተሸንፈህ ብዙ ማውራት አይመከርም።

በማጥቃቱ ስለነበረው ክፍተት

ብዙ ጊዜ ተናግሬዋለሁ፤ ያሉንን አጥቂዎች እነዚህ ናቸው። ከዚህ ውጪ እኔ ገብቼ አልጫወትም ፤ ወይም አንተ አጥቂ ከሆንክ እሞክርሃለው። መጀመርያው የተበላሸው ነገር አሁን ብትናገር ሰሚ አይገኝም። ቡድኑ ጥቂት የአጥቂ አማራጭ ነው ያለው ምንም ማድረግ አይቻልም በዚህ ነው የምንቀጥለው።

\"\"