የአሰልጣኞች አስተያየት| መቻል 2-3 ባህር ዳር ከተማ

\”ውጤቱ አደጋ ለደረሰባቸው ደጋፊዎቻችን መታሰቢያ ይሁንልን\” ደግአረግ ይግዛው

\”በመጀመርያው አጋማሽ የሰራናቸው ስህተቶች ውጤቱን እንዳናገኝ አድርጎናል\” ፋሲል ተካልኝ

ደግአረግ ይግዛው – ባህር ዳር ከተማ

ስለ ጨዋታው

ጨዋታው ጥሩ ነበር። ጨዋታው በመጀመርያው አጋማሽ ለመጨረስ ስራዎች ሰርተናል። የፉዐድ አስገዳጅ ቅያሪም ትንሽ በማጥቃቱ እንድንቀንስ አድርጎናል ፤ በተረፈ ግን ከሽንፈት ነው የመጣነው። መድንም እየተጠጋ ነው እነዚ እነዚ ተጫዋቾቹ ላይ የፈጠረው ጫና ይኖራል። ያንን ሁሉ ተቋቁመን አሸንፈን የወጣንበት መንገድ የሚያስደስት ነው።
ፈታኝ ነበር ፤ ይሄንን ማሳካታችን እጅግ ያስደስታል። ለተጫዋቾቼ እንኳን ደስ አላቹ ማለት እፈልጋለው። ውጤቱም አደጋ ለደረሰባቸው ደጋፊዎቻችን መታሰቢያ ይሁንልን።
\"\"
ስለ ጨዋታ ፉክክር

የዛሬ ዋና ሀሳባችን ቀጣይ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ለምናደርገው ጨዋታ በነጥብ ርቀን አለመገኘት ነበር ፤ ያንን አሳክተናል። ቀጣይም ይሄንን አጠናክረን መቀጠል ነው የምንፈልገው።

ፋሲል ተካልኝ – መቻል

ስለ ጨዋታው

እንደሚመስለኝ የመጀመርያው ጎል ስናስተናግድ ተጫዋቾቻችን መረጋጋት አልቻሉም ነበር ፤ ሁለተኛው ኳስም ወድያው ገባ። የጨዋታው ለውጥ እዛጋ ነበር ብዬ ነው የማስበው። በመጀመርያው አጋማሽ መረጋጋት አልቻልንም። ያገኘናቸው ዕድሎች ያለ መጠቀማችን እንዳለ ሆኖ ተጨማሪ ጎል አለማስተናገዳችንም ዕድለኞች ነን። በሁለተኛው አጋማሽ በመጀመርያው አጋማሽ ያጣነው ለማግኘት የተጫዋቾች ለውጥ አድርገን ነው የገባነው። ያ የተወሰነ ፍሬ አፍርቷል ፤ በመጨረሻም ሙሉ ለሙሉ አጥቅተን ለመጫወት ሞክረናል። በመጀመርያው አጋማሽ የሰራናቸው ስህተቶች ውጤቱን እንዳናገኝ አድርጎናል።
\"\"
ስለ ቡድኑ ወቅታዊ ብቃት

ዛሬ ነጥብ ማግኘት ነበረብን ፤ ወደ አደገኛው ዞን እየወረድን ነው። ያሉትን ቀሪ ጨዋታዎች በትኩረት ተመልክተን አሻሽለን እንቀርባለን።