ቅዱስ ጊዮርጊስ የቅጣት ውሳኔ ተላልፎበታል

የሊጉ አወዳዳሪ በ28ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዙሪያ የዲሲፕሊን ውሳኔን ሲጥል ፈረሰኞቹ የቅጣቱ አካል ሆነዋል።

የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በ28ኛው ሳምንት የፕሪምየር ሊጉን ጨዋታ ተንተርሶ በተደረጉ ጨዋታዎች ላይ ታዩ ባላቸው የዲሲፕሊን ጥሰቶች ዙሪያ የሊጉ የውድድር እና አመራር ኮሚቴ የቅጣት ውሳኔን ሲያስተላልፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከባህር ዳር ጋር የነበረውን ጨዋታ በመንተራስ ቅጣት ተላልፎበታል።

\"\"

ክለቡ በዚሁ ጨዋታ ላይ የክለቡ ደጋፊዎች አወዳዳሪውን አካል እንዲሁም ግለሰብን በተለይ የሚዲያ ባለሞያን አፀያፊ ስድብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት የቀረበባቸው በመሆኑ የክለቡ ደጋፊዎች በዕለቱ ለፈፀሙት ጥፋት እና ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ጥፋት አጥፍተው ከተቀጡት ቅጣት ሊታረሙ ባለመቻላቸው ክለቡ ላይ የሰባ አምስት ሺህ የገንዘብ ቅጣት ተላልፎበታል።

በተጫዋችና ቡድን አመራሮች በኩል በተላለፈ ውሳኔ አስናቀ ተስፋዬ (ለገጣፎ ለገዳዲ) ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያሰጥ ጥፋት በመፈፀሙ ቀይ ካርድ አይቶ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ለፈፀመው ጥፋት አንድ ጨዋታ እንዲታገድ ፣ ተስፋዬ አለባቸው(መቻል) እና በኃይሉ ግርማ (መቻል) በተለያዩ 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ በመመልከታቸው አንድ ጨዋታ እንዲታገዱ እና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍሉ ፣ አብነት ደምሴ (ኢትዮ ኤሌትሪክ) እና ፍቅረየሱስ ተ/ብርሀን (ሆሳዕና ሆሳዕና) በተለያዩ 10 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ በመመልከታቸው ሁለት ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 2000 እንዲከፍሉ ተወስኗል።

\"\"