የሴካፋ ከ18 ዓመት በታች የሴቶች ውድድር ለሁለተኛ ጊዜ ተራዝሟል

በኬንያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው የሴካፋ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ውድድር ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

\"\"

በኬንያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው የሴካፋ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ውድድር ከሰኔ 17 ጀምሮ እንደሚካሄድ ተገልፆ የነበረ ቢሆንም ወደ ሰኔ 22 መሸጋገሩን ሴካፋ ለአባል ሀገራት ማሳወቁ ይታወሳል። ሆኖም ሶከር ኢትዮጵያ ዛሬ ባረጋገጠችው መረጃ መሠረት ደግሞ ውድድሩ በድጋሚ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ ታውቋል። ምናልባትም ከሐምሌ አጋማሽ በኋላ ሊጀምር እንደሚችልም ሰምተናል።

በዚህ ውድድር ላይ እንደሚሳተፉ ያረጋገጡ ሀገራት የሆኑት አዘጋጇ ኬንያ ፣ ኢትዮጵያ ፣ ታንዛንያ ፣ ዩጋንዳ ፣ ቡሩንዲ ፣ ጅቡቲ እና ዛንዚባር መሆናቸው ይታወቃል። የኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለውድድሩ ያለፉትን ሁለት ሳምንታት ዝግጅት በማድረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን ውድድሩ ለሁለተኛ ጊዜ መራዘሙ ደግሞ በቡድኑ ዝግጅት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳይፈጥር ተሰግቷል። አሁን እንዳገኘነው መረጃ ከሆነ ብሔራዊ ቡድኑ ተበትኖ በድጋሚ የውድድሩ ቀን ሲቃረብ እንደሚጠራ ሰምተናል።

\"\"