ሉሲዎቹ የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ያደርጋሉ

የኦሊምፒክ ማጣሪያ ጨዋታ የሚጠብቀው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ያደርጋል።

\"\"

በፓሪስ አዘጋጅነት ለሚስተናገደው የ2024 የኦሊምፒክ ውድድር በአፍሪካ ዞን ማጣርያ ከቻድ ጋር የተደለደለው የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን በልምምድ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል። ላለፉት ስድስት ቀናት በ35 ሜዳ ፣ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እንዲሁም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ልምምዱን ሲያከናውን የቆየው ቡድኑ ሰኔ 30 የአቋም መፈተሻ ጨዋታ እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

ፌዴሬሽኑ በማህበራዊ ገፆቹ ባጋራው መረጃ መሰረት ሉሲዎቹ ጨዋታቸውን ከሲሼልስ አቻቸው ጋር የሚያደርጉ ሲሆን ጨዋታ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እንደሚደረግም ፌዴሬሽኑ ጨምሮ አስታውቋል።

\"\"