የ29ኛው ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች ላይ ማስተካከያ ተደርጓል

የፊታችን ሐሙስ የሚደረጉት ሁለት ጨዋታዎች በዕኩል ሰዓት እንዲደረጉ የውድድርና ሥነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

\"\"

የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 ዓ.ም ውድድር ሊገባደድ የሁለት የጨዋታ ሳምንታት ዕድሜ ብቻ የቀሩት ሲሆን ላለመውረድ የሚደረገው ትንቅንቅ የብዙዎቹን ትኩረት የሳበ ሆኗል። ሆኖም የሊጉ አወዳዳሪ አካል ትናንት ባደረገው ስብስባ መሠረት ድሬዳዋ ከተማ ጨዋታው በተመሳሳይ ሰዓት ይደረግ ብሎ ያቀረበውን አቤቱታ በመቀበል ሐሙስ ሰኔ 22 የሚደረጉት ሁለት ጨዋታዎች በዕኩል ሰዓት እንዲደረጉ ወስኗል።

\"\"

በዚህም መሰረት አርባምንጭ ከተማ ከ ድሬደዋ ከተማ በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታድየም እንዲሁም ወላይታ ድቻ ከ ወልቂጤ ከተማ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ስታድየም ከቀኑ በ09:00 ሰዓት የሚጫወቱ ይሆናል።