የዋልያዎቹ ጨዋታዎች ላይ የቀን እና የቦታ ለውጥ ተደርጓል

በክረምቱ ወደ ሰሜን አሜሪካ እንደሚያቀና የሚጠበቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መርሐ ግብር ማስተካከያ ተደርጎበታል።

\"\"

የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን በክረምቱ ወደ አሜሪካ በመጓዝ ከካረቢያን ሀገራት ጋር የወዳጅነት ጨዋታዎች እንደሚያደርግ ይታወቃል። ይህንን አስመልክቶ የእግርኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ ባወጣው መረጃ መሰረት ብሔራዊ ቡድኑ የሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ተሸጋሽገዋል።

\"\"

ፌዴሬሽኑ ይፋ ባደረገው በዚህ መረጃ መሰረት ከዚህ ቀደም ሐምሌ 1 አትላንታ ላይ ሊደረግ የነበረው የኢትዮጵያ እና ጉያና ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ ሐምሌ 26 በዋሺንግተን ዲሲ ሴግራ ፊልድ ላይ የሚደረግ ሲሆን በተጨማሪም ሐምሌ 29 ከትላንታ ሮቨርስ ክለብ ጋር በአትላንታ ሳውዘርን ክሬሰንት ስታዲየም እንደሚከናወን ታውቋል። ፌዴሬሽኑ የቲኬት እና ሌሎች ዝርዝሮች በቀጣይ እንደሚገለፁም ጨምሮ አስታውቋል።