የ2015 የፕሪምየር ሊጉ እጩ ኮከብ ተጫዋቾች ዝርዝር ታውቋል

በ2015 የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የኮከብ ተጫዋቾች ፣ ኮከብ ወጣት ተጫዋቾች እና ግብ ጠባቂዎች እጩ ዝርዝር ይፋ ሆኗል።

የ2015 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር ሊጠናቀቅ የአንድ ሳምንት ዕድሜ ብቻ ቀርቶታል። በትላንትናው ዕለት ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀድያ ሆሳዕናን በማሸነፍ የሊጉን ዋንጫ ከፍ ማድረግ የቻለ ሲሆን የክለቡ አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ በምርጥ አሰልጣኝነት ዘርፍ እንዲሁም አጥቂው እስማኤል ኦሮ አጎሮ በከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት እንደሚመረጡ ይጠበቃል። በሌላ በኩል የሊግ አክኪዮን ማኅበሩ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ፣ የዓመቱ ምርጥ ወጣት ተጫዋቾች እና የዓመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂዎች ዝርዝርን ይፋ ሲያደርግ ክለቦች እና የስፖርት ቤተሰቡ እንዲመርጥም ጠቁሟል።
\"\"
በምርጥ ግብ ጠባቂነት ዘርፍ – ፔፕ ሰይዶ (ከሀድያ ሆሳዕና ፣ አቡበከር ኑራ (ከመድን) እና ቢኒያም ገነቱ (ከወላይታ ድቻ)

የዓመቱ ምርጥ ወጣት ተጫዋች ዘርፍ – ፍቅሩ አለማየሁ (ለገጣፎ ለገዳዲ) ፣ ዮሴፍ ታረቀኝ (አዳማ ከተማ ፣ አማኑኤል ተርፉ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ዘላለም አባተ (ወላይታ ድቻ) እና አበባየው ሀጂሶ (ወላይታ ድቻ

የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ዘርፍ – ባሲሩ ዑመር (መድን)፣ አለልኝ አዘነ (ባህርዳር ከተማ) ፣ እስማኤል ኦሮ አጎሮ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ቢኒያም በላይ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ፉዓድ ፈረጃ (ባህርዳር ከተማ) ፣ ያሬድ ባዬ (ባህርዳር ከተማ) እና ጌታነህ ከበደ (ወልቂጤ ከተማ)
\"\"