አርባምንጭ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ቅጣት ተላለፈባቸው

በ29ኛው ሳምንት የፕሪምየር ሊጉ ጨዋታዎች ላይ በነበሩ የዲሲፕሊን ጥሰቶች ዙሪያ የሊግ አክሲዮን ማህበሩ የውድድር አመራር የቅጣት ውሳኔን አሳልፏል።

የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ29ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ላይ በታዩ የዲሲፕሊን ግድፈቶች ዙሪያ ላይ የሊጉ የውድድር እና ስነ ሥርዓት ኮሚቴ አመራር ባደረገው ስብስባ በክለቦች እና ተጫዋቾች ላይ የቅጣት ውሳኔን አሳልፏል።

\"\"

አርባምንጭ ከተማ በድሬዳዋ 1-0 በተረታበት ጨዋታ የቡድኑ ደጋፊዎች የጨዋታ አመራሮችን አፀያፊ ስድብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት የቀረበባቸው በመሆኑ ክለቡ ሰባ አምስት ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍል ሲወሰንበት ሲዳማ ቡና በለገጣፎ ለገዳዲ 3-2 ሲረታ ከጨዋታው አስቀድሞ በነበረው ቅድመ ስብሰባ ላይ የቡድን መሪው አለመገኘታቸውን ተከትሎ ክለቡ አምስት ሺህ ብር እንዲቀጣ በሊግ አክሲዮን ማህበሩ ተላልፎበታል።

በተጫዋች ላይ በተወሰደ ቅጣት የለገጣፎው ማሊያዊ አጥቂ ሱለይማን ትራኦሬ ቡድኑ ሲዳማን ሲረታ ግብ ጠባቂው አዱኛ ፀጋዬን በመማታቱ በቀይ ካርድ መወገዱ የሚታወስ ሲሆን አራት ጨዋታ እንዲታገድ ሦስት ሺህ የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍል ሲወሰንበት በተመሳሳይ የሀዋሳው ተከላካይ በረከት ሳሙኤል በባህር ዳሩ ጨዋታ ላይ ፍፁም ጥላሁን ላይ በሰራው ጥፋት በሁለተኛ ቢጫ ካርድ በቀይ በመወገዱ አንድ ጨዋታ እንዲታገድ ሲወሰንበት ፣ እንየው ካሳሁን (ድሬደዋ ከተማ) ፣ እያሱ ለገሰ (ድሬደዋ ከተማ)፣ ተባረክ ሄፋሞ (ሀዋሳ ከተማ) እና ዓለምብርሀን ይግዛው (ፋሲል ከነማ) በተለያዩ 5 ጨዋታዎች የቢጫ ካርዶችን በመመልከታቸው 1 ጨዋታ እንዲታገዱ እና አንድ ሺ አምስት መቶ ብር እንዲከፍሉ ተወስኗል።

\"\"