የትግራይ እግርኳስ ፌዴሬሽን ቅሬታ አቅርቧል

የትግራይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በክልሉ ክለቦች ላይ የተወሰነው ውሳኔ ላይ ያለውን ቅሬታ አቀረበ።

\"\"
የትግራይ እግር ኳስ ፌደሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የወሰነው ውሳኔ ላይ ቅሬታ እንዳለው ዛሬ በፃፈው ደብዳቤ ገልጿል። ፌዴሬሽኑ የወሰነው ውሳኔ በትግራይ የነበረውን ሁኔታ እና የጉዳዩን ክብደት ከግምት ያላስገባ እንዲሁም ከተደረሰው የሰላም ስምምነት ጋር የሚጋጭ መሆኑን ጠቅሶ ውሳኔው የክለቦቹን እና የህዝቡን ስነ-ልቦና የሚጎዳ በመሆኑ ውሳኔው በድጋሜ እንዲጤን  ጠይቋል።

\"\"
በተጨማሪም በቀጣይ ቀናት ከክለቦቹ ጋር በመመካከር የጋራ ውሳኔ እንደሚያስተላልፉ አመላክቷል።

ከስር ደብዳቤው ተያይዟል 👇

\"\"