ንግድ ባንክ ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾች አስፈርሟል

ኢትዮጵያን ወክሎ በሴካፋ ዞን የቻምፒየንስ ሊግ ማጣሪያ ውድድር የሚሳተፈው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የአራት ነባሮችንም ውል አድሷል።
\"\"
በኢትዮጵያ የሴቶች እግር ኳስ ላይ ባለፉት ዓመታት ነግሶ የተቀመጠው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግን በተከታታይ ሻምፒዮን መሆኑን ተከትሎ ዘንድሮም ኢትዮጵያን ወክሎ በመድረኩ ላይ ተሳታፊ ለመሆን ከነገ ጀምሮ በሀዋሳ ከተማ ዝግጅቱን ይጀምራል። በአሰልጣኝ ብርሀኑ ግዛው የሚመራው ቡድኑ የሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር ሲያገባድድ የአራት ነባሮችን ውል አድሷል።
\"\"
በቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ መቻል እና የተጠናቀቀውን ዓመት በኤሌክትሪክ ያሳለፈችው ግዙፏ ተከላካይ መሠሉ አበራ ፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ በአማካይ እና በአምበልነት ስታገለግል የቆየችው ሶፋኒት ተፈራ እና የአርባምንጭ ከተማዋ የመሐል ተከላካይ ድርሻዬ መንዛ የክለቡ አዳዲስ ፈራሚ ተጫዋቾች ሲሆኑ በሁለተኛው ዙር ቡድኑን የተቀላቀለችው የመስመር ተጫዋቿ ፋና ዘነበ ፣ ግብ ጠባቂዎቹ ታሪኳ በርገና እና ንግስቲ መዓዛ እንዲሁም አጥቂዋ መዲና ዐወል በክለቡ ውል ያደሱ ሌላኛዎቹ ተጫዋች ሆነዋል።