ንግድ ባንክ የመጀመሪያ ፈራሚውን አግኝቷል

አዲስ አዳጊው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመስመር አጥቂ በሁለት ዓመት ውል በይፋ አስፈርሟል።
\"\"
ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 2009 ላይ ከወረደ በኋላ ለመፍረስ የተገደደው እና በ2014 ዳግም ወደ ውድድር በመመለስ በተጠናቀቀው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀን በበላይነት በማጠናቀቅ ወደ ሀገሪቱ ትልቁ የሊግ ዕርከን መመለስ የቻለው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአሰልጣኝ በፀሎት ልዑልሰገድን ውል ከማራዘሙ በፊት የመጀመሪያ ፈራሚው በማድረግ አጥቂው ኪቲካ ጀማን በሁለት ዓመት የውል ኮንትራት እንዳስፈረሙ አሰልጣኙ በተለይ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ከኢትዮጵያ ቡና ወጣት ቡድን ከተገኘ በኋላ በከፍተኛ ሊጉ ገላን ከተማ ከአሰልጣኝ በፀሎት ጋር መስራት የጀመረው ተጫዋቹ በመቀጠል ወደ ኢትዮጵያ መድን 2014 ላይ ከመራ በኋላ በተመሳሳይ ከአሰልጣኙ ጋር ቡድኑን ወደ ፕሪምየር ሊጉ ማሳደግ ችሏል። በተጠናቀቀውም ዓመት በመድን የሁለተኛ ዓመት ቆይታውን ካደረገ በኋላ ለሦስተኛ ጊዜ ከአሰልጣኙ ጋር ለመስራት በሁለት ዓመት ውል የክለቡ ቀዳሚው ፈራሚ ሆኗል።
\"\"
ክለቡም በቀጣዮቹ ቀናት በርከት ያሉ ዝውውሮችን እንደሚፈፅምም ሰምተናል።